About

History

ሚድዌስት የኢትዮጵያ ወንጌላዊ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት

የመጀመሪያ ስብሰባውን ከሦስት አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕመናንና መሪዎቻቸው በተገኙበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 ዓ,ም, በሂውስተን ከተማ ላይ አደረገ። በዚህ ስብሰባ ላይ ተካፋይ የነበሩት ሦስት አብያተ ክርስቲያናት በካንሳስ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስቲያን ፣ በሂውስተን የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስቲያንና ፣ በዳላስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ባፕቲስት ቤተክርስቲያን ናቸው።

ይህ ስብሰባ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዓመት አንድ ጊዜ ለአራት ተከታታይ ቀናት ለአባላቱ አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ  እየተካሄደ ይገኛል። ስብሰባው መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ የኅብረቱን አባልነት ያገኙ የአብያተ ክርስቲያናት ቁጥር ከሦስት ወደ ስምንት የጨመረ ሲሆን የተካፋይ ምዕመኑም ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት ትልቅ ዕድገት እያሳየ መጥቷል።

የስብሰባው ይዘትና ጥራት ፤ አዘገጃጀቱና አቀራረቡ በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ምዕመናን በየፈርጁ የሚያካትት ሲሆን መንፈሳዊ ሕይወትን በማነፅ ፣ ወገኖችን በክርስቶስ ፍቅር በማቀራረብና በማስተሳሰር በምዕመናኑ ልብ ውስጥ ዘወትር የሚታወስ ልዩ ጊዜን ያመቻቸ ስብሰባ መሆኑ በግልፅ የሚታይ ነው።

Mission

ዓላማ

“ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ . . .

እኛም አንድ እንደሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ

አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ . . .”

 ዮሐንስ 17፥21 – 23

“ይሁን እንጂ. . . በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ 
በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ።”

ፊልጵስዩስ 1፥27

አላማዎች፦

1ኛ) በሰሜን አሜሪካ ሚድዌስት time zone ላይ በሚገኙት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል መቀራረብና አንድነት መፍጠር። ይህን ኅብረት ልዩ የሚያደርገው ኅብረቱ የሚያተኩረው በመሪዎች ላይ ሳይሆን በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል ስለሆነ የመሪ ለውጥ በሚኖርበትም ጊዜ ኅብረቱ ቀጣይነት ይኖረዋል።

2ኛ) በአብያተ ክርስቲያናቱ ምዕመናን መካከል የበለጠ መቀራረብ ለመፍጠር በአመት አንድ ጊዜ ሁሉም አባላት የሚገኙበት የመነቃቂያ ኮንፍራንስ በማዘጋጀት ጌታን አንድ ላይ መፈለግ፣ ማምለክና ወቅታዊ ትምህርቶች መስጠት። በተጨማሪም ማዕድ አብሮ በመቁረስ፤ እርስ በርስ በመወያየት የሞቀ አንድነት እንዲለማመዱ ማድረግና የጌታን እራት አብሮ መውሰድ።

3ኛ) በየጊዜው የሚነሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሁኑ ትምህርቶች በጋራ ለመከላከል ትክክለኛውን ትምህርት ማስተማርና ተገቢውን እርማት መስጠት።

4ኛ) ለአገልጋዮች በየከተማው ስለሚካሄደው የወንጌል ስርጭት ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን መስጠትና የአሠራር ልምዶችን መለዋወጥ።

5ኛ) የጋራ የሆኑ የሚሽን ስራዎችን በኢትዮጵያና በሌሎችም ስፍራዎች ማካሄድ።

6ኛ) በመካከላችን ያሉትን ጸጋዎች ለመከፋፈል እንድንችል  አገልጋዮችን መለዋወጥ።

7ኛ) ወጣቶቻችን በአንድ ላይ እንዲገናኙ፣ እንዲተዋወቁና የአገራቸውን ባህሎች እንዲረዱ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።

8ኛ) በተለያየ ዕድሜ ክልል ለሚገኙት ታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች መንፈሳዊ ቅስቀሳና ስልጠና በማድረግ ተተኪውን ትውልድ ለእግዚአብሔር ስራ ማዘጋጀት።

9ኛ) መሪዎች በአመት አንድ ጊዜ ተገናኝተው አብረው እንዲጸልዩ፣ የእግዚአብሔርን ስራ በተመለከተ እንዲወያዩና ለሚመጣው አመት ዕቅድ እንዲያወጡ እግረ መንገዱንም የመሪዎቹ ስብሰባ በሚደረግበት ከተማ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመነቃቂያ ፕሮግራም ማካሄድ።

Member Churches

Ethiopian Christians Fellowship Church in Houston

Ethiopian Christians Fellowship Church in Houston

Dr. Tesfa Workeneh, Sr. Pastor

401 Present Street, 
Missouri City, Texas 77489

Tel: 713-484-5530    
Fax: 713-484-5526

Web: www.ecfchouston.org

Ethiopian Evangelical Church in Dallas

Ethiopian Evangelical Church in Dallas

Dr. Bedlu Yirga, Sr. Pastor

2822 S Jupiter Rd,
Garland, TX 75041

Tel: 214-703-0100
Fax: 713-484-5526

Web: www.eecdallas.org

Ethiopian Evangelical Baptist Church of Irving

Ethiopian Evangelical Baptist Church of Irving

Dr. Abera Mitku Sr. Pastor

3640 W. Northgate dr., 
Irving, TX 75062

TEL. 972-762-7982

Web: www.eecii.org

 

The Redeemer of the World Evangelical Church

The Redeemer of the World Evangelical Church

Tesfaye Seyoum, Sr. Pastor

9116 Lackland Rd  
St. Louis, MO 63114

Tel: 314-395-9799
 Fax: 314-853-4568

Web: www.rwecstl.org

 Ethiopian Christians Fellowship Church in Kansas

Ethiopian Christians Fellowship Church in Kansas

Henok Tsegaye, Sr. Pastor

14345 W 119th St,
Olathe, Kansas, KS 66062

Tel: 913-254-7450

Web: www.ecfcks.org

Ethiopian Christians Fellowship Church in Austin

Ethiopian Christians Fellowship Church in Austin

Melaku Teketel, Sr. Pastor

3106 E 14th 1/2 St, 
Austin, Texas, TX 78702

TEL. 512-550-1273/512-473-9905

Web: www.eeccaustin.com

 

Ethiopian Evangelical Church in Oklahoma

Ethiopian Evangelical Church in Oklahoma

Dr. Tesfahun Hatia, Sr. Pastor

770 7th Street East, 
St. Paul, MN 55106

TEL. 651-772-0234 ex 20

Web: www.reect.org

 

El-Shaddai International Ethiopian Church

El-Shaddai International Ethiopian Church

Mekuriachew Kassa, Sr. Pastor

13622 W 62nd Street
Shawnee , Kansas 66062

TEL. 913-486-9546

Web: www.eliec.org

 

Ethiopian Evangelical Church Allen, Texas

Ethiopian Evangelical Church Allen, Texas

Bruke Solomon, Sr. Pastor

1309 E Main Street
Allen, TX 75002

TEL. 214-881-4496

Web: www.eecallen.org